ሰላም፡ ለብዙ አመታት ከኤችአይቪ ጋር መኖር ማለት የጤና ችግሮችን መቋቋም ማለት አይደለም። በተቃራኒው፣ ዛሬ ባለው የስለጠነ የመድሃኒት ሕክምና፣ ብዙውን ጊዜ ጤናን የመጨረሻው የሚያሳስብ ነገር ነው። ከኤችአይቪ ጋር አብሮ የሚኖር ሰው የዕድሜ ርዝማኔ ከጤናማ ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው፣ እንዴውም አንዳንዶች በቅርብ የሕክምና ክትትል ምክንያት ከዚያ በላይ ኖው ይላሉ።
ስለዚህ ይህንን ሥር የሰደደ የጤና ችግርን ለመቋቋም የሚሰጠው ትኩረት ከጤና ወደ የህይወት ጥራት ተሸጋግሯል። ረጅም ዓመታት መኖር ብቻ በቂ አይደለም ፣ ጥሩ ፣ ደስተኛ እና ደህና ሕይወት መኖር ይገባቹዋል። መብቶችዎን ማወቅ እና ስለመብታቹን መቆም አስፈላጊ ነው። ባለሙያዎችን ተያገዙ እና ሁኔታዎን በሚመለከቱ የሕክምና ውሳኔዎች ውስጥ ይሳተፉ እና ድጋፍ ሰጪ አካባቢን ይጠብቁ።.
ከሌሎች ከኤችአይቪ ጋር አብረው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር እንድትገናኙ እና እርስዎም እርስዎ አካል እንዲሆኑ እና እንዲረዱዎት ከሚወደው ማህበረሰብ ጋር ለመገናኘት፡ እኛ እዚህ በኮሚቴው ውስጥ በየዓመቱ ዝግጅቶችን፣ ጉዞዎችን፣ ኮንፈረንሶችን እና የዕረፍት ጊዜዎችን ለአዎንታዊው ማህበረሰብ እና በተለይም ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት እናዘጋጃለን።
እርስዎም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር በልባም እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ እንዲሳተፉ በደስታ ንጋብዛቹው ኣለን።
ምክንያቱም ብቻቹ የምትጋፈጡበት ምንም ምክንያት የለም።
Mail: POZ@aidsisrael.org.il
WhatsApp: 0543200071